You are here: HomeSermonየቤተ ክርስቲያን አባልነቴን በምንም ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ማቋረጥ የለብኝምን?

የቤተ ክርስቲያን አባልነቴን በምንም ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ማቋረጥ የለብኝምን?

Written by  Thursday, 04 September 2014 00:00

ኅበራዊ ግንኙነት ትልቅ ጥንቃቄ የሚሻ ጕዳይ ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም በየደረጃቸው የሚገኙ ማኅበራዊ መስተጋብሮች ደማቅ መስመርና ጠንካራ ዳር ድንበር ስለተበጀላቸው የየግነኙነቶቹ ዳር ድንበሮች በውል ይታወቃሉ፡፡ ክልሎቹን መጣስ ከነውርነት ባለፈም በሕግ ሊያስቀጣ ሲበዛም ዘብጥያ ሊያስወረውር ይችላል፡፡ ከዚህ የተነሣም እነዚህን መከልክሎች ጥሶ የሚሄድ ወፈፌ እንብዛም አይታይም፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ምዕራባውያን ግላዊነት” (individualism) በመባል የሚታወቀውን የኑሮ ዘዬ መቀለሳቸው፣ መስመር ስቶ የመጋጨቱ አባዜ በከፍተኛ ቊጥር እንዲቀንስ ምክንያት የሆነ ይመስለኛል፡፡ ሁሉም በጠበሉ ነዋ ማን በማን ላይ ይደርሳል?

 

ዎች የራሳቸው የሆነ ፍላጎት፣ ጠንካራና ደካማ ጐን፣ የሕይወት ተሞክሮ፣ የዕውቀት ደረጃ፣ የኑሮ ዐላማና ግብ፣ ዐመልና ጠባይ፣ ልምድና ባህል ወዘተረፈ ያላቸው አካላት ናቸው፡፡ ታዲያ የሰው ልጅ ይህ ዐይነቱ ልዩነቶች ካሉት፣  አንድነትና ኅብረትን የጕዞ መስመሩ አድርጎ ሊጓዝ እንዴት ይችላል? ቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቲያኖች አንድነትንና ኅብረትን እንዲኖራቸው ማዘዙ ብቻ ሳይህን፣ የክርስቲያኖች ኅብረትና አንድነት በአንድ አካል አካል ላይ እንዳለ ብልት ይመስለዋል፤ ይህም አንድነቱ ጠንካራ መሆኑን ብቻ ሳይሆን አንዱ ብልት ያለሌላው ብልት ህልውና ሊኖረው እንደማይችል የሚያሳስብ ነው፡፡ ታዲያ የሰው ልጅ እንዲህ ዐይነቱ ልዩነት እያለው ይህን የመሰለ አንድነት እንዲፈጥር መጠበቁ የችግሩን ጡዘት ይበልጥ የሚያነዝረው ይመስላል፡፡ 

 

ንድነትና ኅብረት ብርቱ ፈተና የተጋረጠበት ማኅበራዊ ግንኙነት ቢሆንም፣ የማይጨበጥ የረቂቅ ፍልስፍናዊ ነባቤ ቃል ግን አይደለም፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክህነታዊ ጸሎቱ፣ እኛ [ማለትም አብና ወልድ] አንድ እንደ ሆንን፣ እነርሱም [ማለትም ደቀ መዛሙርት] አንድ ይሆኑ ዘንድ(ዮሐንስ 17) የሚለው የተማጽኖ ጸሎቱ አንድነትና ኅብረት በአጸደ ሥጋ ለሚኖሩ ሰብአውያን እውን መሆን የሚችል ጕዳይ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ረዳት ይሆነን ዘንድ ጌታ የላከልን መንፈሰ ጽድቅ ጵራቅሊጦስም፣ ክርስቲያናዊ አንድነትና ኅብረት እንድንመሠርት ረዳት እንደሚሆነንም ቅዱስ ቃሉ ያስተምረናል (ዮሐንስ 14-17)፡፡ ይህ እውን ከሆነ ደግሞ፣ ከብረት ይጠነከረ አንድነት ከነሐስ የበረታ ኅብረት መመሥረት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ተስፋውን የሰጠን እግዚአብሔር ቃሉን ለመፈጸም ታማኝ ነውና፡፡  

 

አጠቃላይ ኅብረትና አንድነት ከሞት የበረታ ፍቅር፣ የራስን ፍላጎትና ጥቅም የሚሠዋ መሥዋዕታዊ የሕይወት ዘዬ፣ ብልኅነትን የተሞላ የቤተ ክርስቲያን አመራር፣ ጠንካራ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት፣ በጾምና በጸሎት የሚጸና የመንበርከክ ሕይወት፣ የራስን ጥቅምና ፍላጎት መሥዋዕት ለማድረግ የቈረጠ መሥዋዕታዊ ሕይወት ይፈልጋል፡፡

 

ዎች ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያላቸውን መስተጋብበር አስመልክተው ከሚጠይቁኝ ጥያቄዎች መኻል፡–   

  • በርግጥ አንዲት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባል መሆን አለብኝን?”  
  • በርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ የአንዴት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባል እንድንሆን የስተምራልን?”
  • የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባልነቴን ማቋረጥ የምገደድባቸው ቅድመ ሁኔታዎች አሉን?”
  • አባል የምሆንባትን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የምመርጠው በየትኛው መስፈርት ነው?”

 

ነዚህንና እነዚህ መሰል ጥያቄዎች በአጥጋቢ መልኩ ለመመለስ ቅድሚያ ሰጥተን ልንጠይቀው የሚገባ መሠረታዊ ጥያቄ ያለ ይመስላኛል፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያንን በምድር ላይ ያኖረበት ዐቢይ ምክንያት ምንድን ነው?” የሚለው ጥያቄ ነው፡፡

 

ዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቊረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር(ሐዋርያት ሥራ 2÷42) የሚለው ምንባብ፣ ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ የመመሥረቷ ዐላማ ከሆኑት ውስጥ አራት መሠረታውያን ነገሮችን ይዘረዝራል፡፡ (1) በሐዋርያት ትምህርት መታነጽ፣ (2) ከቅዱሳን ጋር ኅብረት ማድረግ፣ (3) የጌታን ራት መካፈል፣ (4) በጀማ ጸሎት በኅብረት መትጋት ናቸው፡፡ ይህ ከአንድ ምንባብ የምናገኘው ትምህርት ነው፡፡ የነገረ መለኮት ምሁራን ሃያ ሰባቱን የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በጥልቀት በመመርመር የቤተ ክርስቲያንን ቀዳማይ ተልእኮ አራት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ይኸውም፡– 

 

  1. እግዚአብሔርን ማምለክ (ለምሳሌ የሚከተሉትን ምንባባት ይመለከቷል፤ ሉቃስ 4÷8፤ ዮሐንስ 4÷23፤ ራእይ 4÷10)
     
  2. ራስን ማነጽ (ለምሳሌ፤ ኤፌሶን 4÷14፤ ሮሜ 12÷1015÷14)
    • ራስን ማነጽ በሚለው ነጥብ ውስጥ የሚካተቱ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ እርስ በርስ መዋደድ (1ዮሐንስ 3÷11)፤ ለሌሎች ርኅራኄን ማሳየት (ኤፌሶን 4÷32)፤ ጸሎት (ሐዋርያት ሥራ 2÷42)፤ ከወገኖች ጋር ጠንካራ ኅብረት ማድረግ (ሮሜ 12÷10)፤ መማማር (ሮሜ 15÷142ጢሞቴዎስ 2÷151ቆሮንቶስ 4÷6)፤ መሠረተ እምነትን ከመናፍቃን መጠበቅ (ፊልጵስዩስ 1÷16)፤ አማኞችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ (ማቴዎስ 18÷15-17)፤ በአጠቃላይ ወደ ክርስቶስ ሙሉት ለማደግ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ሁሉ ማከናወን (ኤፌሶን 4÷15-16)፡፡    

  3. ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ መስበክ (ለምሳሌ፤ ማቴዎስ 28÷18-20፤ ሐዋርያት ሥራ 1÷81ጴጥሮስ 3÷15)

  4. ክብረ ሠናይ ሥራዎችን ማከናውን (ያዕቆብ 1÷27)፡፡ 

ነዚህ ነገሮች ሁሉ አንድ ግለሰብ በራሱ የሚከውናቸው ነገሮች እስካልሆኑ ድረስ፣ የቤተ ክርስቲያን አባልነት ወሳኝ ጕዳይ መሆኑ አያሟግትም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች መታዘዝ እንዳለብን (ዕብራውያን 13÷171ጢሞቴዎስ 5÷17) በአንጻሩም ሽማግሌዎች መንጋውን በሥርዐት መምራት አንዳለባቸው (1ጴጥሮስ 5÷1-5፤  ሐዋርያት ሥራ 20÷29-30)፣ ከሥነ ምግባር የጐደሉ አባላት በተግሣጸ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መውደቅ እንደሚያስፈልጋቸው (1ቆሮንቶስ 5÷1-12)፣ መበለቶችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንዴት መንከባከብ እንዳለብን ወዘተ ሲገልጽ (1ጢሞቴዎስ 5÷3-16)፣ የቤተ ክርስቲያን አባልነትን ታሳቢ አድርጎ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባልነት እውን ካልሆነ እነዚህ ነገሮች በምንም መልኩ እውን መሆን አይችሉም፡፡ 

ቅርቡ ለአንድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሰዎች ቤተ ክርስቲያናቸውን ለምን ይለቃሉ? የሚል ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ የተሰጠኝ መልስ የሚከተለው ነው፡–(1) የግለሰቡ የግል ፍላጎት፤ ለምሳሌ ልጆቻቸው ወጣቶች የሚበዙበት ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ መፈለጋቸው ወላጆችም እነርሱን ለመከተል ይገደዳሉ፤ ጠንካራ የሕፃናትና የጎልሞሶች የሰንበት ትምህርት ቤተ ፍለጋ የሚለቁም ወላጆች አሉ፡፡ ከፒያኖ ይልቅ በኦርጋን ለመዘመር በመፈለግ አባልነታቸውን ያቋረጡ ሰዎችም አሉ፡፡ (2) ጥሩ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ያለመኖር፤ ለምሳሌ አንጎበኝም አስታዋሽ የለንም ወዘተ የሚለው አቤቱታ በመጨረሻ ቤተ ክርስቲያን በመልቀቅ ይደመደማል፡፡ (3) የማገልገል ዕድል ማጣት፤ በተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎች ውስጥ ለማገልገል ፈልገው ዕድሉን ያጡ ሰዎች አባልነታቸውን እንዳቋረጡ ተነግሮኛል፡፡ (4) ጠብና ቊርሾ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመራከት ቤተ ክርስቲያንን ጥሎ ለመሄድ ምክንያት ሆኗል፡፡  

 

ነዚህ በአሜሪካን አገር ሰዎች የቤተ ክርስቲያን አባልነታቸውን የሚቀይሩባቸው ምክንያቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ቃለ እግዚአብሔር በየትኛው ምክንያት ነው አባልነታችንን እንድንተው የሚያስተምረን? ዋና ዋና የሚባሉትን ምክንያቶች ልዘርዝር፡፡ 

  1. አስተምህሮአዊ ምክንያት፤ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በስሕተት ትምህርት ላይ ቈራጥ አቋም ከሌላቸው ወይም የተሳሳተ ትምህርትን እያዩ እንዳላዩ ሆነው የሚያልፉ ከሆነ፣ የቤተ ክርስቲያን አባልነታችንን ማቋረጥ የግድ ይኖርብናል (ሮሜ 16÷17ገላትያ 1÷8)፡፡ ቃለ እግዚአብሔር መመሪያችን ከሆነ እንደ ቃሉ ያልሆኑ ትምህርቶች ሁሉ ውጉዝ ናቸው፡፡ ስሕተት ትምህርቶችን የምታስተምር ወይም የተሳሳተን ትምህት የሚያስተምርን ወገን ሃይ በማትል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አባል መሆን የለብንም፡፡ ክርስቲያናዊ ትምህርቶችን ዐቢይና ንዑስ ብለን የምንከፍል ሲሆን፣ በጥቃቅን አስተምህሮዎች ላይ የተለያየ አቋም ቢኖረን ስሕተት ላይሆን ይችላል፡፡ አንድ ለመሆን አንድ ዐይነት መሆንን የግድ ላይፈልግ ይችላልና፡፡


  2. ሥነ ምግባራዊ ምክንያት፤ ተግሣጸ ቤተ ክርስቲያንን ችላ የምትል ቤተ ክርስቲያን፣ አባል መሆን አይኖርብንም (1ቆሮንቶስ 5 1ተሰሎንቄ 3÷614)፡፡ በኀጢአት የሚመላለሰውን ሰው መከፋፈልን በአማኞች መኻል የሚዘራውን ሰው ቤተ ክርስቲያን ከምግባሩ በንስሓ እንዲመለስ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊው ነገር ሁሉ ማድረግ ይኖርባታል፡፡ አልመለስ ያለወን ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን አባልነት ማባረር  መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ ይህ ዐይነቱ ተግሣሥ ግለሰቡ በንስሓ እንዲመለስ ከማድረጕም በላይ ሌሎች የእርሱን መንገድ እንዳይከተሉ ትምህርት ይሰጣል፡፡


  3. ክርስቲያናዊ ሕይወት መጠውለግ፤ ደቀ መዛሙርትን ለማፍራት፣ ወንጌልን ለማሠራጨት፣ ለጸሎት እንዲሁም በማኅበረሰቡ ውስጥ ግብረ ሠናይ ምግባሮችን ለማከናውን ዕቅድም ሆነ ዐላማ በሌላት ቤተ ክርስቲያን አባል መሆን አይኖርብንም (ለምሳሌ፤ ማቴዎስ 28÷18-20፤ ሐዋርያት ሥራ 1÷81ጴጥሮስ 3÷15፤ ያዕቆብ 1÷27)፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን በዚህ ምድር እንድትኖር አምላክ የፈቀደበት ምክንያት ጐድሏልና፡፡

 

ለቀን በመሄዱ ከቈርጥን ማድረግ የሚገባን ነገሮች

  1. በድካምም፣ በብርታትም በታማኝነት ያገለገሉንን ሰዎች ከልብ ማመስገን ይኖርብናል፡፡
  2. የምንልቅበትን ዐቢይ ምክንያት በግልጽ ማሳወቅ ጥሩ ሊኖን ይችላል፡፡ ምናልባት ቤተ ክርስቲያኒቱ እኛ ካለፍንበት መጥፎ ተሞክሮ ትምህርት ልትቀስም፣ ወደ ፊት ስሕተቷን ልታርም ትችል ይሆናልና፡፡ 
  3. የበደሉንን ይቅር ማለት የበደልናቸውንም ይቅርታ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
  4. ሕይወት በሳር ብቻ ሳይሆን በአሳርም የምንማርበት የትምህርት ተቋም ናትና ከዚህ ተሞክሮ ምን ትምህርት አገኘው የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡         

 

ማጠቃለያ

ዎች ፍጹማን እንዳልሆኑ ሁሉ ፍጹም የሆነች ቤተ ክርስቲያንም አለች ብሎ መገመት ስሕተት ነው፡፡ ፍጹም አይደለንም ማለት ደግሞ የሰይጣን ቊራጭ መሆን አለብን ማለትም አይደለም፡፡ ይህ እውን በሆነበት ምድር ነገሮችን በኾደ ሰፊነት መመልከቱ ሚዛናዊ የክርስቲያናዊ ሕይወት ዘዬ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ሰዎች በአስተምህሮአዊ ስሕተት፣ በሥነ ምግባር ውድቀት እንዲሁም በክርስቲያናዊ ሕይወት በመርገፍ ችግር ምክንያት አባል የሆንባትን ቤተ ክርስቲያን ትተን መሄድ እንችላለን፡፡ እንወያይበት፡፡   

 ኦ አብ በእንተ ኢየሱስ ርዳአነ፤

ኦ ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ማኅረነ፤

ኦ ጵረቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ሥረይልነ ኀጣዊነ፤ አሜን፡፡ 

Read 10471 times Last modified on Friday, 05 September 2014 08:17
Tesfaye Robele

ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ በኢንተርናሽናል የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የአዲሱ መደበኛ ትርጒም ተርጓሚ ሆኖ ሠርቶአል፡፡ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የቤተ እምነቱ የሥነ ጽሑፍ ክፍል ኀላፊና የ“ቃለ ሕይወት” መጽሔት ዋና አዘጋጅ ሆኖ አገልግሎአል፡፡ ለዐቅብተ እምነት አገልግሎት ካለው ትልቅ ሸክም የተነሣ፣ ተስፋ ዐቃብያነ ክርስትና ማኅበርን መሥርቶአል፤ በዐቅብተ እምነትም ላይ በርካታ መጻሕፍትን አዘጋጅቶአል፡፡ የዶክትሬት ዲግሪውንም የሠራው ለረጅም ዓመት በሠራበትና ወደ ፊትም በስፋት ሊያገለግልበት በሚፈልገው በክርስቲያናዊ ዐቅብተ እምነት (Christian Apologetics) አገልግሎት ነው፡፡

Website: www.tesfayerobele.com Email This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 221 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.